አምላኬ ያደረገውን ነገር ባወራው
የኢትዮጵያ መሠረተክርስቶስ በ1943 ዓ.ም. የተመሠረተች ሲሆን የአዲስ አበባዋ አጥቢያ ዘግየት ብላ በ1953 ዓ.ም. በኦሎምፒያ አካባቢ ስትጀመር የቦሌ አካባቢ የለማ ስላልነበረ የምእመኑ ቁጥር ከ30 አይበልጥም ነበር።በቤተክርስቲያኒቱ የታሪክ መጽሐፍ ላይ እንደተመለከተው ‹‹ የጊዜው ቤተክርስቲያን መሪዎች ሚሲዮናውያንን ጨምሮ ሁኔታው ስላሳሰባቸው በየሳምንቱ አርብ ማታ በራሱ በፀሎትቤቱ በመሰብሰብ በቤተክርስቲያኒቱ ጌታ መነቃቃትን እንዲጀምርና ከተማውን በመንፈስቅዱስ እሳት እንዲያቀጣጥለው ይፀልዩ ነበር።››